የሲቪል  ቤተሰብ  ምዝገባ  አገልግሎት

 በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረማርያም ከሰም ወረዳ  አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብይ ዮሐንስ የሲቪል ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት  ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አደረጉ

በወረዳው የሲቪል ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ተግባር በትኩረት ይዞ መከናወን እንዳለበት ተገለፀ።

በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረማርያም ከሰም ወረዳ የሲቪል ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የጥቅምት ወር የስራ አፈጻጸም ግምገማና የቀጣይ አቅጣጫ የተቀመጠበት መድረክ የተካሄደ ሲሆን በዚህ የግምገማ መድረክ ላይ የሲቪል ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎትን ኮሚቴዎች በተሳተፉበት የጥቅምት ወር ስራ አፈፃፀሙ በጥልቀት የተገመገመና በቀጣዩም በትኩረት ይዞ መከናወን እንዳለበት አቅጣጫ ተቀምጧል።

የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት የሲቪል ቤተሰብ ምዝገባ በድን መሪ አቶ ገነነ ጥሩነህ በጥቅምት ወር በዘርፉ የተከናወኑ ተግባራትን በጥንካሬና በእጥረት አቅርበው ካስገመገሙ በኋላ አያይዘው እንደገለፁት ሲቪል የቤተሰብ ምዝገባ ማለት በአንድ ሰው ላይ ከልደት እስከ ሞት የሚከሰት ተፈጥሯዊ ማህበረሰባዊ የአቋም ለውጥ ጠቋሚ ክስተት በመሆኑ የሰዎችን የማንነት ህጋዊ መሠረት ለመጣል ሲቪል የቤተሰብ ምዝገባ ጠቀሜታን ማወቅና መመዝገብ በትኩረት ይዞ መስራት አለበት ብለዋል።

የወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ አብይ ዮሐንስ በበኩላቸው ማህበረሰባችን ሲቪል የቤተሰብ ምዝገባ ጥቅምን ከዚህ በላይ በመረዳትና በማስረዳት በመረጃ እና በማስረጃ ላይ ተመስርቶ ዜጎች የሚታወቁባትን ሀገር ለመፍጠር የሁሉም ባለድርሻ አካል ተግባር በመሆኑ ለዚህ መሳካት የወረዳው አመራርና ሁሉም ባለ ድርሻ አካላት ወደ ስራው ገብቶ መረባረብ አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የመድረኩ ተሳታፊ ኮሚቴዎች በሰጡት ሀሳብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ዜጎች በፍትሃዊነት ማግኘት እንዲችሉ ለማድረግ እና ዜጎች ሲቪል የቤተሰብ ምዝገባ በወቅቱ እንዲያስመዘግቡ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ እና ህጋዊነት ወይም አስገዳጅ የሆነ የምዝገባ ስርዓት የተዘረጋ በመሆኑ የሚመለከታቸው ኮሚቴዎችና ባለድርሻ አካላት ለተገባሩ ውጤታማነት በትብብር መስራት ይገባቸዋል በሚል ሀሳባቸውን ሰጥተዋል።

1 thought on “የሲቪል  ቤተሰብ  ምዝገባ  አገልግሎት”

Leave a Reply to admin Cancel Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top