የወሳኝ ኩነቶች የምዝገባ ቦታ አይነቶች፦
▷የልደት ምዝገባ ቦታ
▷የጋብቻ ምዝገባ ቦታ
▷የፍች ምዝገባ ቦታ
▷የሞት ምዝገባ ቦታ
✅የልደት ምዝገባ ጠቀሜታ፦
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
➔የማንነት ህጋዊ መሰረት ለመጣል
➔ወላጆችን ለማወቅ
➔ቤተሰባዊ ዝምድናን ለማወቅ
➔የአሳዳጊን ማንነት ለመለየት
➔የመታወቅ ህጋዊ መብትን ለማረጋገጥ
➔እድሜን መሰረት በማድረግ የተወሰነ እድሜ ሲደርስ የሚሰጡ
የአገልግሎት መብቶችን ለመጠየቅ
➔ትምህርት ቤት የመገንባት መብት ለማግኘት
➔በስራ ለመሰማራት /ስራ የመቀጠር/ ፍቃድ ለማግኘት
➔መውረስ እና ንብረት የማስተዳደር መብቶችን ለማግኘት
➔በሰራዊት አባልነት ለማገልገል ወይም ከአባልነትለመገለል
➔የነዋሪነት ወይም የማንነት መታወቂያ ለመጠየቅ
➔የመምረጥና መመረጥ መብትን ለመጠየቅ
➔ካለ እድሜ ጋብቻ ለመጠበቅ
➔የህፃናትን ጉልበት ብዝበዛ ለመከላከል
የሞት ኩነት ምዝገባ ጠቀሜታዎች፦
➣ለሟች ቀሪ ዘመዶቻቸው ሟቹ ለመሞት ህጋዊ መረጃ በመሆኑ
ውርስ የሚገባቸው የመውረስ ጥያቄ ለማቅረብ
➣የኢንሹራንስ ጥያቄ ለማቅረብ
➣የቤተሰብ ድጎማ ጥያቄ ለማቅረብ
➣በህይወት ለሚኖረው የትዳር ጓደኛ የማግባት ፍቃድ ለማግኘት
የጋብቻ ኩነት ምዝገባ ጠቀሜታዎች፦
➛ጋብቻው ህጋዊ መሆኑን ለማረጋገጥ
➛የተጋቢዎችን ዝምድናና ግንኙነት ህጋዊነት ለማረጋገጥ
➛የጋብቻ ውጤት ለሆኑ ህፃናት በቤተሰብ የመጠበቅ ህጋዊ መብት
ለማረጋገጥ
➛ህጋዊ ወራሽነትን ለማረጋገጥ
➛ጋብቻ በሚፈርስበት ጊዜ የልጆች አስተዳደግን ለመወሰን
➛ወደ ውጭ ሀገር ለማጓጓዝ ፓስፖርት የማግኘት ፍቃድን ለማቅረብ
➛የልጆች ህጋዊነት ለማረጋገጥ
የፍች ኩነት ምዝገባ ጠቀሜታዎች፦
➨ፍች ለመፈፀም ህጋዊ ማረጋገጫ ለመሆን
➨ለተፋችዎች እንደገና የማግባት መብት ለማግኘት
➨ከፍች በኋላ የንብረት ክፍፍል ለማድረግ
➨ከፍች በኋላ ስለተወለዱ ልጆች ህጋዊ መረጃ ለማግኘት
➨ከፍች በኋላ በአንዳቸው ላይ ከሚመጡ የገንዘብ ወይም የንብረት ጥያቄዎች /እዳ/ ነፃ ለመሆን
ከመንግስት አንፃር የሚያስገኘው ጠቀሜታ፦
✔️ቀልጣፋና ውጤታማ የፍትህ ስርዓት ለማስፈን
✔️አስተማማኝ የስነ ህዝብና የጤና ስታስቲክስ ለማግኘት
✔️ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎቶችን ፍትሀዊ ለማድረግ
የወሳኝ ኩነት የምዝገባ የጊዜ ገደብ፦
➾ልደት በተከሰተ #በ90 ቀናት ውስጥ መመዝገብ አለበት
➾ሞት በተከሰተ #በ50 ቀናት ውስጥ መመዝገብ አለበት
➾ጋብቻ፣ፍች ኩነቶች በተከሰቱ #በ30 ቀናት ውስጥ መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
የወሳኝ ኩነት ምዝገባ መርሆዎች፦
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
△ያለማቋረጥ/continuity /
△ቋሚነት / permanence/
△አስገዳጅነት /compulsoriness/
△ሁሉን አቀፍ/universality/