
ለሾላ ገበያ ከተማ ነዋሪዎች የንፁህ መጠጥ ዉሀ አገልግሎት በአጭር ጊዜ ለመስጠት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳዉ አስተዳደር ምክር ቤት አስታወቀ።
ለወረዳዉ ዋና ከተማ ሾላ ገበያ ከተማ ዘለቄታዊነት እና አስተማማኝነት ያለዉ የንፁህ መጠጥ ዉሀ አገልግሎት ለመስጠት ወደ ስራ የተገባ ሲሆን የHDPE ጎማ ዝርጋታ ጉድጓድ ቁፋሮ በጠቅላላ መንግስት ሰራተኞች የቁፋሮ ስራ ተሰርቷል።
የወረዳዉ አስተባባሪ አመራሮች የልማቱ ተሳታፊዎችን ከስራዉ ጋር በተያያዘ እና ቀጣይ ሊተገብሯቸዉ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ አወያይተዋል።
ወረዳዉ በበጀት ዓመቱ በርካታ መሰረተ ልማቶችን እየሰራ ሲሆን አንዱ የሾላ ገበያ ከተማ ነዋሪዎችን ዘለቄታዊነት ያለዉ የንፁህ መጠጥ ዉሀ አገልግሎት በአጭር ጊዜ ለመስጠት በትኩረት አየሰራ እንደሆነ እና ስራዉ በወረዳዉ መንግስት በጀት እና በሾላ ገበያ ከተማ ነዋሪዎች ተሳትፎ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል።
በሾላ ገበያ ከተማ የንፁህ መጠጥ ዉሀ አገልግሎት እየተሰጠ ቢሆንም የጃንባሪያ ወንዝ ዳገታማ በመሆኑ የዉሀ መሳቢያ መሳሪያዎች በተደጋጋሚ ለብልሸት በመጋለጣቸዉ ወረዳዉ ላልተገባ ወጭ እየተዳረገ ነዉ የተባለ ሲሆን የጃንባሪያ ወንዝን በሚስጥር ወንዝ ለመተካት የተፋጠነ ስራ እየተሰራ ነዉ ተብሏል።
መንግስት ሰራተኞች የመንግስት ስራን በአግባቡ ከመስራት በተጨማሪ በዉሀ ስራዉ ላይ ሚናቸዉን ሊወጡ እንደሚገባ የተገለፀ ሲሆን በጉልበት፣በገንዘብ እና በሌሎች ዘርፎች ላይ የበኩላቸዉን ሊወጡ ይገባል ተብሏል።