የታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል

በሰሜን ሸዋ ዞን ሀገረ ማርያም ከሰም ወረዳ የታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በደብረ-ፅጌ ቀበሌ አበይድላ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በታላቅ ድምቀት ተከበረ።

በሰማዕቱ ቅዱስ ጊዮርጊስ ተራዳዒነት የተገኘውን የጥቁር ህዝቦች የፃነት 1መቶ 30ኛውን የዓድዋ ድልን በመዘከር በየዓመቱ የካቲት 23 ቀን የሚከበር ታላቅ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ በዓል ሲሆን በዘንድሮውም ዓመት በርካታ ህዝበ ክርስቲያን ከሩቅም ከቅርብም ተሰባስበው ባከበሩት አመታዊ ክብረ በዓል ላይ ሊቃውንት አባቶች ፣ በሰንበት ትምህርት ቤት ተማሪዎች እና መዘምራን በያሬዳዊ ዝማሬ በማዜም ፍፁም ሰላማዊ በሆነ የዓል ድባብ በድምቀት ተከብሮ ውሏል።

በንግስ ፕሮግራሙ ላይ በእንግድነት የተገኙ ሊቃውንት የሀይማኖት አባቶች አመታዊ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ በመርሃ ግብሩ ላይ ለተገኙት ህዝበ ክርስታያን የስብከተ ወንጌል ትምህርትና አባታዊ አስተምህሮት አድርገው ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን በሰለም እንዲጠብቅ፣ ሀገራችን ሰላም እንድትሆንና የምህረት እንዲሰጠን በሚል ጸሎት ተደርጎ ታቦታቱ ወደ መንበራቸው በሰላም ገብተው የበዓሉ ፍጻሜ ሆኗል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top